Freedom4Ethiopian.WordPress.com: በአዲስ አበባ ትግሉ ከታሰበዉ በላይ ከቁጥጥር ዉጭ እየሆነ ነዉ::

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Wed, 5 Oct 2016 01:07:51 +0200

በአዲስ አበባ ትግሉ ከታሰበዉ በላይ ከቁጥጥር ዉጭ እየሆነ ነዉ::

አዲስ አበባ ለቀጣዩ ህዝባዊ ስርአት ቄጠማ እየጎዘጎዘች ለበሰበሰዉ ዘሰኛ የአሸባሪ ቡድን ህወአትም እሳት ለኩሳለች:: ከህወአታዊያን ወጭ ሁሉም በአንድነት አዲስ አበባ የገዳዮች መቀመጫ ላይ ተነስቷል:: ተኩስ በመላዉ አዲስ አበባ እየተሰማ ነዉ:: ሁሉም ነገር ቆሟል የጥይትና የአምቡላንስ ድምፅ ብቻ ነዉ የሚደመጠዉ::

ህዝቡ መንገዶችን ሁሉ እየዘጋ የወያኔ ንብረቶችን በማዉደም ላይ ነዉ:: ተናግረን ነበር ህዝብን አትናቁ ብለን:: ዉርድ ለራስ ብለን::

አመራር የተባለ ህወአታዊ የተባለ ሁሉ መግቢያ መዉጫ አጥቷል:: ሁሉም በእግሩ ወደየመኖሪያዉ እየተሯሯጠ ነዉ::

አዎ የግፈኞች መጨረሻ የከፋ ነዉ ብለን መክረን ነበር:: መጨረሻችሁ እየከፋ ነዉ:: ለህዝብስ ያዉም ለኛ ሞት አብሮን ኖሯል::

የተጎዱ የተገደሉም እንዳሉ መረጃዎች እየመጡ ነዉ:: እስካሁን አራት ስዎች በአንድ አካባቢ ብቻ ተገለዋል::

ከብስራተ ገብርኤል ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ጀምሮ ዘነብወርቅ፣ አየር ጤና፣ አለምባንክ፣ አለም ገና ባሉ አካባቢዎች ከትላልቅ ሆቴሎች ጀምሮ ሁሉም የንግድ ድርጅቶች ተዘግተዋል፡፡ ወጣቶች ተቃውሞውን እያስፋፉ ከአየር ጤና ጋር ለማገናኘት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ተቃውሞውን ለመቀላቀል ሁሉም በንቃት እየተጠባበቀ ነው፡፡

Received on Tue Oct 04 2016 - 17:46:55 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved