Zehabesha.com: በከፍተኛ ምስጢር የተያዘው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ ሳብያ በአ.አ. ከፍተኛ የሰራዊት ክምችት ይታያል

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Mon, 26 Sep 2016 15:50:04 +0200
በከፍተኛ ምስጢር የተያዘው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ ሳብያ በአ.አ. ከፍተኛ የሰራዊት ክምችት ይታያል

26 ሴፕቴምበር 2016 (EMF) በከፍተኛ ምስጢር የተያዘው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ ሳብያ በአዲስ አበባ በተለይ ደግሞ በአራት ኪሎ አካባቢ ከትላንት ምሽት ጅምሮ ከፍተኛ የሰራዊት ክምችት ይታያል።

feteshaከትላንት ማምሻ የጀመረው ፍተሻ አሁንም እንደቀተለ ሲሆን የአጋዚ ሰራዊት አላፊ አግዳሚውን በማሸበር እና በመፈተሽ ላይ እንደሚገኝ የአይን ምስክሮች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። የአይን ምስክሮች እንደሚሉት መሃል አዲስ አበባ- የገዢው ፓርቲ መቀመጫ ኣራት ኪሎ አካባቢ ውጥረቱ የከፋ ይመስላል። በአካባቢው ይሰማ የነበረው የተኩስ ልውውጥ በዚያው በቤተ-መንግስት እንደሆነም ይነገራል። የከባድ መሳርያው ጩኸት እንደተሰማ በከፊል አዲስ አበባ መብራት እንዲጠፋ ተደርጎ እነደነበርም ከስፍራው ያነጋገርናቸው እማኞች ገልጸዋል።

አለም አቀፍ እና የግል መገናኛ ብዙሃን በተከለከሉበት በአሁኑ ሰዓት በጨለማ እየተደረገ ያለውን ሁሉ ለማጣራት ቢቸግረም – አንደኛ በኢሃዲግ ድጅቶች መካከል ሁለተኛ ደግሞ በሕወሃት ከፍተኛ አመራር እና መካከለኛ ካድሬዎች መሃል የከረረ አለመግባባት እንዳለ እየተሰማ ነው። የዚህ የጥቅም እና የሃሳብ ልዩነት እየሰፋ መጥቶ ወደ ከፍተኛ ፍልሚያ ሊያመራ እንደሚችል የሚገምቱም ጥቂቶች አይደሉም።

በሃገሪቱ ያሉ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እስካሁን ድረስ እንዳይከፈቱ ትእዛዝ ተሰጥቷል። የትምህርት ቤቶችን የልብ ትርታ ለማዳመጥ በመምህራን የተጀመረው ስብሰባ ውጤት ገዥው ፓርቲ እንደጠበቀው አልሆነም። የመምህራኑ ቁጣ እንዲህ ከበረታ የተማሪዎቹ የከፋ እንደሚሆን በመገንዘባቸው ትምህርት በቶችን የመክፈቱ አደጋ ስጋት ውስጥ ከትቷቸዋል።

በፊታችን የሚከበሩ ሁለት በዓላት (የመስቀል እና የእሬቻ በዓላት) አከባበርም ገዥውን ፓርቲ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።

አገዛዙ በአካባቢ እና ፌደራል ፖሊስ አባላት ላይም እምነት በማጣቱ የአጋዚ ሰራዊቱ እና ታማኝ ደህንነት አባላት ብቻ ናቸው ፍተሻውን እና ግድያውን እያካሄዱ ያሉት።

በኤርትራ ጠረፍ (ባድመ) ላይ ተሰማርቶ የነበረው የህወሃት ሃይል አካባቢውን ለቅቆ ወደ አዲስ አበባ እና ጎንደር እንዲዘምት ተደርጓል።

የሕዝብን ውጫዊ አካል ሊፈትሹ ይችላሉ – የሸፈተ ልቡን ግን ለመፈተሽ አይቻላቸውም። ወከባው ችግሩን ያባብሰዋል እንጂ አይፈታውም።

Received on Mon Sep 26 2016 - 08:34:10 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved