Goolgule.com: “ይቺ ሀገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ እኛ አድማጭ እናንተ ተናጋሪ የምትሆኑበት አካሄድ ማክተም አለበት” የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የመጀመሪያ ቀን የውይይት ውሎ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Tue, 20 Sep 2016 14:46:45 +0200

“ይቺ ሀገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከተፈለገ እኛ አድማጭ እናንተ ተናጋሪ የምትሆኑበት አካሄድ ማክተም አለበት”

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የመጀመሪያ ቀን የውይይት ውሎ
aau-meeting
 
 

በዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ካሳ ተ/ብርሀን አጠቃላይ የውይይት መድረኩ መነሻ አሳብ ትረካ እና የእለቱ የውይይት አጀንዳ በሆነው ያለፉት 25 ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ጉዞ ዙሪያ የሚያጠነጥን ገለፃ በኋላ በምርጦቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተነሱ አስተያቶች እና የአካሄድ ጥያቄዎች:-

1. የመጀመሪያ ተናጋሪ፡-

1.1 “የዚህ ወይይት አጀንዳ ከጠበኩት በታች ወርዶብኛል በወላይቲኛ አንድ አባባል አለ – ያቺ እንትን’ኮ ወደቀች ቢሏት፤ ቀድሞም አቀማመጧ ለመውደቅ ነው አለች”፡፡

1.2 “ካሳ! አንተ ሚኒስትር ነህ በዛ ላይ የዩኒቨርሲቲያችን የቦርድ ሊቀመንበር በዚህ ሁሉ ኃላፊነት ውስጥ ሆኖ PhD candidate መሆን አይቻልም ስለዚህ ስራህን ልቀቅ”

1.3 “ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ይምጣና ያወየን፣ እናንተ ውረዱና ከእኛ ጋር ተቀመጡ”

2. ሁለተኛ ተናጋሪ

2.1 “ይቺ ሀገር አንደ ሀገር አንደትቀጥል ከተፈለገ እኛ አድማጭ እናንተ ተናጋሪ የምትሆኑበት አካሄድ ማክተም አለበት፣ በዚህ ስብሰባ አኛ የእናንተን እንከን እናውራ እናንተ ደግሞ ዝም ብላችሁ አድምጡን”፡፡

3. ሦስተኛ ተናጋሪ

3.1 “የዛሬ ዓመት በተመሳሳይ የውይይት መድረክ ብዙ ቁም ነገሮች ተነስተው ነበር ነገር ግን አንዳቸውም ሳይተገበሩ ዛሬ ደግመን ተገናኘን”

3.2 “አቶ ካሳ የመንግሰት ስልጣን ይዘህ ለግል ጥቅምህ በማዋል የዩኒቨርስቲውን ህግ ጥሰህ PhD candidate ሆነሐል”

3.3 “ውይይቱን የመምራት ሞራል የለህም”

የአቶ ካሳ መልስ፡-

ካሳ ተ/ብርሀን

ካሳ ተ/ብርሀን

1. “እኔ ውይይቱን የመምራት ችግር የለብኝም፣ ከእኔ የምትበልጡ ትልልቅ ምሑራንና ባለዕውቀቶች እንደላችሁ እሙን ነው ነገር ግን በአጋጣሚ የቦርድ ሰብሳቢ ሆኜ እስከተቀመጥኩ ድረስ ወይይቱን የመምራት ኃላፊነት አለብኝ”

2. “ይህ የውይይት መድረክ በመላ ሀገሪቱ ባሉ የትምህርት ተቋማት የሚደረግ እና መድረኩም አንዲመራ የተያዘለት ፕሮግራም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይሆን በቦርድ ለቃነመናብርት ነው”

3. “አኔ ብማር ክፋቱ ምንድን ነው? እኔም’ኮ አንድ ዜጋ ነኝ፣ ትምሀርት የመጀመሩን እድል አግኝቼ ነበር ነገር ግን ጊዜ በማጣት ምክንያት ብቻ class attend ባለማድረጌ ለመቀጠል አልቻልኩም፣ ጊዜ ሲኖረኝ ግን ታሰተምሩኛላችው”

በመቀጠልም ከተሰብሳቢ ምሁራን አንዱ አጁን በማውጣት ማሳሰቢያ እንዳለው ተናገረ፤ አንዲናገር ዕድሉ ሲሰጠውም “በመጀመሪያ ይሄ ስብሰባ ሲጀመር በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በኮንሶ በአልሞ ተኳሾች ለተገደሉ ንፅሑን ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ሊሆን ይገባ ነበር” በዚህ ጊዜ የስብሰባው አዳራሽ ለረጅም ደቂቃ ባልተቋረጠ ጭብጨባ ተስተጋባ ሲቀጥልም “ሁሌም ተደጋጋሚ አጀንዳ ነው ይዛችው የምትመጡት ካችአምና የትምህርት ጥራት አምና እና ዘንድሮም የትምህርት ጥራት ምንም አዲስ ነገር የለም፣ ለዚህ ስበሰባ የተመደበው በጀት ተቀንሶ በተለያዩ ክልሎች በተነሱ ግጭቶች የቤተሰባቸውን አባላት ላጡ ወገኖች ይሰጥ ለእኛ የሶስት ቀን ውይይት ይበቃናል”

* ቀጣይ ተናጋሪ

“ሰው አየሞተ እና ህዝብ ለተቃውሞ እየወጣ political crisis ውስጥ ገብተን ስለትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት መወያየት አኔን ያሳፍረኛል”

“ታልሞ የተመጣው ነገር ለኢቢሲ ዜና የሚሆን ነገር ለመቃረም ነው”

* ሌላ ተናጋሪ

“Next time I don’t want to see these board members (አቶ ካሳን ጨምሮ መድረኩን እየመሩ ያሉትን የዩኒቨርሲቲውን የቦርድ አባላት ነው)

“ዶ/ር አድማሱ ባለፈው ጊዜ አሜሪካን ሀገር ውስጥ በሱፐር ማርኬት ውስጥ የደረሰብዎትን አይተናል እነርሱ እዛ ወላፈኑ ገና ለገና ይደርስብናል ብለው ይህን ካደረጉ አኛስ እዚህ እንፋሎቱ ውስጥ የምንቀቀለው ምን እናድርግ?” (ፎቶ: ለማሳያ የተወሰደ)

(መስከረም 9፣ 2009 ዓ.ም)
(ሱራፌል ሐቢብ)

Received on Tue Sep 20 2016 - 07:25:50 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved