Ethsat.com: በአንባጊዮጊስ በወታደሮችና በህዝቡ መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 16 Sep 2016 23:41:27 +0200

በአንባጊዮጊስ በወታደሮችና በህዝቡ መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

September 16, 2016

Watch these news:

ESAT Daily News Amsterdam September 16, 2016

http://video.ethsat.com/?p=28466

ESAT Weekly News Digest 16 Sep 2016

http://video.ethsat.com/?p=28481

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ አምባጊዮርጊስ ከተማ አቀርቢያ በምትገኘው አይባ ኪዳነምህረት መሳሪያቸውን ላለማስጠነቅ ትግል የጀመሩት አርሶአደሮች ፣ ከወታደሮች ጋር ተፋልመው በርካቶችን ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል። አንዳንድ ወገኖች የሟች ወታደሮችን ቁጥር በአስራዎች ይቆጠራል ይላሉ።  ኢሳት  የሟች ወታደሮች ትክክለኛ አሀዝ ለማወቅ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ትናንት ምሽትና ዛሬ ጠዋት በርካታ ወታደሮች ወደ ወደ አካባቢው መንቀሳቀሳቸው በህዝቡና በወታደሮች መካከል የሚካሄደው ውጊያ እየሰፋ መምጣቱን የሚያመላክት ነው። በህዝቡ በኩል እስካሁን አንድ ሰው መገደሉን ለማወቅ ተችሎአል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከሁለት ሳምንት በፊት በባህርዳር ዙሪያ አንዳሳ ቀበሌ አካባቢ በወታደሮች እና በአርሶአደሮች መካከል የተደረገውን ውጊያ መርተዋል የተባሉ ሰዎችን ለመያዝ የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል። 8 የመንግስት ወታደሮች በተገደሉት በዚህ ውጊያ ተሳትፈዋል፣ ህዝቡንም መርተዋል በሚል የተጠረጠሩ አርሶአደሮችን የአካባቢው ፖሊሶች አታለው ለመያዝ ሲሞክሩ፣ አርሶአደሮቹ “እጃችንን ለእናንተ አንሰጥም፣ መሳሪያችንንም አናስረክብም፣ ይህን ከምናደርግ ተዋግተን እንሞታለን “ በማለት ሊይዙዋቸው የመጡትን ፖሊሶች መልሰዋቸዋል።

እነዚሁ አርሶአደሮች በባህርዳር ተካሄዶ የነበረውን ከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ እንዲሁም በተቃውሞው ተሳትፈዋል የተባሉ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ወደ እስር ቤት በመሄድ ያስፈቱ ናቸው።

*********************************************************************************

በጎንደር ከተማ ቅዳሜ ገበያ ላይ የደረሰው ቃጠሎ ሆን ተብሎ መፈጸሙን ነዋሪዎች ገለጹ

September 16, 2016

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ትናንት ሃሙስ ምሽት በጎንደር ከተማ ቅዳሜ ገበያ በሚባለው አካባቢ የተነሳው ቃጠሎ በርካታ ንግድ ድርጅቶች አውድሟል። ነጋዴዎች ቃጠሎው ሆን ተብሎ መነሳቱን እና እሳቱን ለማጥፋት ህዝቡ ወደ አካባቢው ሲጠጋ መከልከላቸውን እንዲሁም የእሳት አደጋ መኪና ዘግይቶ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በቃጠለው ሰለወደመው የንብረት መጠን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

*********************************************************************************

ገዢው ፓርቲ በሶማሊያ እና በኦሮሞ ብሄሮች መሃከል ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ ነው ሲል የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር አስታወቀ

September 16, 2016

መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ካለፈው ዓመት ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን የጠየቁ ዜጎች የኦሮሚያ እና አማራ ብሔረሰቦችን ጨምሮ በተለያዩ የአገርቱ ዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የኦጋዴን ነጻነት ግንባር አስታውሷል። በዜጎች መሃከል የእርስበርስ እልቂት እንዲፈጠር ሆን ተብሎ በገዥው ፓርቲ እየተሰራ ሲሆን፣  በተለይ በሶማሊያና ኦሮሞ ብሔረሰቦች መሃከል ግጭት በመፍጠር ሰላማዊ ዜጎች ተገለዋል፣ ተሰደዋል፣ በግፍ ታስረዋል።

በሶማሊያና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ወሰኖች አቅራቢያ ነፍጥ የታጠቁ የልዩ ሃይል ጦር አባላት በዜጎች ላይ እልቂት እየፈጸሙ ነው። በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ሕዝባዊ እንቢተኝነት ተከትሎ የልዩ ጦር አባላት በሰላማዊ ሰልፈኞቹ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። የሶማሌ ክልል ጦር አባላት ከክልሉ አልፈው በሰሜን ሶማሊያ፣ ጅቡቲ ውስጥ በሚኖሩ የአማራና የኦሮሞ ብሔረሰብ ሰራተኞች ላይ ኢ-ሰብዓዊ የሆኑ ሰቆቃዎችን እያደርሱባቸው ሲሆን፣  ይህም በመንግስት የተቀነባበረ ሴራ ለቀጠናው ስጋት መፍጠሩን የኦጋዴን ነጻነት ግንባር ገልጿል።

በኦጋዴን አንዳንድ ከተሞች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞና አማራ ብሔር ተወላጆች በመንግስት ወታደሮች እና የአካባቢ ሚኒሻዎች ተገለዋል፣ ከሕግ አግባብ ውጪ በጅምላ ታሰረዋል፣ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። በምስራቅ አፍሪካ ጎረቤት አገራት ተሰደው የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ድሃ የቀን ሰራተኞች ጭምር በህወሃት/ኢህአዴግ የተቀነባበረ ሴራ ከአገራቸው ውጪም ሰቆቃ እየተፈፀመባናቸው መሆኑን ግንባሩ አስታውቋል። ይህንን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በማውገዝ የተቃወሙ የሶማሌ የሃይማኖት አባቶች፣ አዛውንቶች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በፀጥታ ኃይሎች ተደብድበዋል። ይህም ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ በሶማሌ ብሄረሰብና በሌላው የኢትዮጵያ ብሔሮች መሃከል ግጭትና ጥላቻ እንዲፈጠር በማድረግ በኅብረተሰቦች መሃከል ኅብረት እንዳይኖር ለማድረግ መሞከሩን ያመላክታል።

“የኦጋዴን ሕዝብ  ይህን የከፋፍለህ ግዛ ሴራን የሚያውቀው ሲሆን ምንጊዜም በብሔራቸው ይሁን በእምነታቸው መብታቸውን ካጡና ከተጨቆኑ ዜጎቻችን ጎን ይሰለፋል ። የኢትዮጵያ መንግስት ከ2007 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በኦጋዴን ሕዝብ ላይ የጦር ወንጀል መፈጸሙን ቀጥሎበታል። በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች  ተገለዋል፣ ተፈናቅለዋል አድራሻቸው የማይታወቁም የክልሉ ነዋሪዎች አሉ። ይህ ሁሉ በደል እየተፈጸመ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኦጋዴን ነጻነት ግንባር የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮችና የአካባቢው ሚኒሻዎች መጪውን ዘመን በማሰብ ከእኩይ ድርጊታቸው ታቅበው ከሕዝባቸው ጎን እንዲሰለፉ ጥሪውን ያቀርባል።” ብሎአል።

ግንባሩ  ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በህወሃት/ኢህአዴግ የሚመራውን አንባገነኑን ስርዓት መደገፉን እንዲያቆምም ጠይቋል። የአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች ይህንን የተዳከመ ገዥ አካል ድጋፍ እንዳያደርጉ ማሳሰብ ጀምረዋል። ግንባሩ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት የሚያሳትፍ ስርዓት ለመመስረት በሚደረገው ትግል ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጋር እንደሚሰራና ለለውጡ ዜጎች በጋር እንዲነሱ ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

 
Received on Fri Sep 16 2016 - 16:20:32 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved