Zehabesha.com፡ “አንድ ኢትዮጵያ የሚል መንግስት ከመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርሱ ይበላላል” – በአውስትራሊያ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam59_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Tue, 6 Sep 2016 18:42:54 +0200

“አንድ ኢትዮጵያ የሚል መንግስት ከመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እርስ በርሱ ይበላላል” – በአውስትራሊያ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ባለስልጣናት በየቀኑ እውቀታቸውን የሚያስገምት ቃለምልልስ በመስጠት ላይ ናቸው:: ከዚህ ቀደም የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ አማራውን እና ኦሮሞውን እሳትና ጭድ ሲል ነበር:: ዛሬ ደግሞ በአውስትራሊያ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም ኢሕ አዴግ ወርዶ አንድ ኢትዮጵያ የሚል መንግስት ከመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበላላል አለች:: የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱ ሚስት የሆነችው ትርፉ በሕወሓት ክፍፍል ወቅት ወሬ ከነስዬ አብርሃ እየለቀመች ለነመለስ ታመላልስ ነበር እየተባለች በሕወሓት ካድሬዎች ትታማ ነበር::ለዚህም ውለታዋ መለስ ሹመት ሰጥቷት ነበር:: የትግራይ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሃላፊና የክልሉ ዳኞች ሰብሳቢ የነበረችው የዛሬዋ አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማሪያም በሙስና ተገምግማ የነበረ ቢሆንም ሳትከሰስ ወደ አውስትራሊያ እንደሄደች ይነገራል:: ስለወልቃይት; ኮ/ል ደመቀ; ጃዋር መሐመድና ታማኝ በየነ አሳፋሪ ነገር ተናግራለች:: ለጠቅላላ እውቀት ያድምጧት::

ቃለ-ምልልስ፡ https://www.youtube.com/watch?time_continue=227&v=3IbJN9kcsH4

Received on Tue Sep 06 2016 - 11:21:59 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved