Ethsat.com: ኢህአዴግ አባላቱንና የመንግስት ሰራተኞችን ስብሰባ እየጠራ ስርዓቱን ከመናድ ታደጉት እያለ ነው

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 19 Aug 2016 00:47:22 +0200

ኢህአዴግ አባላቱንና የመንግስት ሰራተኞችን ስብሰባ እየጠራ ስርዓቱን ከመናድ ታደጉት እያለ ነው

August 18, 2016

Watch this news:

ESAT Daily News Amsterdam August 18,2016Save Changes

http://video.ethsat.com/?p=27263

ESAT Daily News DC Thu 18 August 2016 Ethiopia

ነሃሴ  ፲፪ ( አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ የመንግስት ሠራተኞችን በወቅታዊ  የጸጥታ ጉዳይ ዙሪያ እያነጋገረ ቢሆንም፣ የመንግሥት ሰራተኛው ድጋፍ ሊሰጠው አለመቻሉን ከያቅጣጫው የሚደርሱን ሪፖርቶች ያሳያሉ። በውይይት ወቅት የኢህአዴግ አባል ያልሆኑ ሠራተኞች በሁሉም የውይይት መድረኮች ላይ በአብዛኛው አስተያዬትና ሃሳብ ከመስጠት ዝምታን መርጠዋል።

የኢህአዴግ አባሎች በስብሰባዎች ላይ “ህዝቡ እኛን  አድምጦ መልስ ከመመለስ ይልቅ ‘እናንተ ለህዝቡ አሳቢ ሆናችሁ ሳይሆን የወያኔ አቃጣሪና ተላላኪ ናችሁ!’ እያሉ ያጥላሉናል፤ ሂዱ ከዚህ ይሉናል! ከህዝቡ ጋር መግባባት አልተቻለም” የሚሉ የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች ተስፋ የሚያስቆርጡ ሃሳቦችን እያቀረቡ ነው።

የኢህአዴግ አመራሮች በስብሰባዎች ላይ ሁሉ ህዝቡ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ለጸጥታ ሃይሎእ እንዲያመለክቱ ተማጽነዋል ።

ኢህአዴግ ለእያንዳንዱ የድርጅቱ አባል (ህዋስ) ለውይይት ያዘጋጀው ሰነድ የደረሰን ሲሆን፣ ሰነዱ “በቅርቡ በአማራ እና በኦሮምያ በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በኦነግና በግንቦት7 አስተባባሪነት በሻቢያና በሌሎች የውጭ ሃይሎች አዝማችነት የተካሄደ ነው” ብሎአል።

ኢህአዴግ አባላቱ የተደቀነውን አደጋ በቀላሉ እንዳያዩት እና አምርረው እንዲታገሉት ያሳስባል። “ ጉዳዩ ተራ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ሳይሆን ከውስጥና ከውጭ በጸረ ሰላም ሃይሎች አስተባባሪነት በሃይል ( በነውጥ) ስርዓቱን ለመናድ ህገመንግስቱን ማፍረስ የጠባብ ሃይሎችና የትምክት ሃይሎች በአንድነት እኛን ኢህአዴግንና አባል ድርጅቶችን በብሄር በመከፋፈል እርስ በእርሳችን በማጋጨት እንድንዳከም፣ አገሪቱን በመበታተን በአገራችን ሰላም እንዳይኖር ማድረግ ነው” ሲል ኢህአዴግ የገጠመውን አደጋ አባላቱ እንዲረዱለት ይጠይቃል።

ሰነዱ በመጨረሻም “ መላው አባላችን አሁን በአገራችን እየተቃጣብን ያለውን የጸረ ሰላም ሃይሎች እኩይ ተግባር ድርጅትና ኢህአዴግ ጋር በተለመደው ቁርጠኝነት በመሰለፍ ህዝባችን አገራችን ከብተና የማዳን ታሪካዊ ሃላፊነት ተጥሎባችሁዋል።” ብሎአል።

Received on Thu Aug 18 2016 - 17:26:26 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved