Goolgule.com: ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ለመመለስ ህወሃት እየመከረ ነው: ህወሃት ግድያ እንዲያቆም ከጌቶቹ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጠው

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Thu, 18 Aug 2016 17:19:12 +0200

ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ለመመለስ ህወሃት እየመከረ ነው

ህወሃት ግድያ እንዲያቆም ከጌቶቹ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጠው
ethiopia police soilders
 
 

* “ብልጡን ባለ ራዕይ መሪ” ክፉኛ ናፍቋል!

የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር /ህወሃት/ አመራሮች ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ከመግደልና ከማስገደል እንዲታቀቡ ታዘዋል። ግድያው የሚቀጥል ከሆነ ከወትሮው በተለየ ርምጃ እንደሚወሰድ ተነግሯቸዋል። “ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ብንመልስ ይሻላል” በሚሉና “አንመልስም” ሲሉ በሚቃወሙ መካከል ክርክር የጀመረው ህወሃት ስምምነት ሊደርስ አልቻለም። ሁኔታው መለስን ከመቃብር ቀስቅሷል።

አባይ ጸሃዬ፣ ሳሞራ የኑስና ሌሎች ባለስልጣናት አሜሪካ እንደነበሩ ለጎልጉል ጠቁመው የነበሩት የመረጃው ምንጮች እንዳሉት ባለስልጣናቱ ግድያ እንዲያስቆሙ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለዋል። በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ያሳሰበው ህወሃት በተመሳሳይ አሜሪካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ ጫና እንድታደርግ ጠይቀዋል። ለዚህም ይመስላል በአሜሪካ በኩል የተቀናቃኝ ድርጅት መሪዎችን በተናጠል ማነጋገር ተጀምሯል።

ህወሃት በግድያው ከገፋበት ከአሜሪካ በኩል የሚሰጠው ምላሽ እንደ ወትሮው በኤምባሲ ወይም በህዝብ ግንኙነት በኩል እንደተለመደው “ጉዳዩ አሳስቦናል” የሚል ተራ መግለጫ እንደማይሆን ማረጋገጫ መሰጠቱን ጎልጉል የሚያምናቸው የዲፕሎማት ምንጮች ከአሜሪካ ተናግረዋል። እንድ መረጃ አቅራቢዎቹ ቀጣዩ የአሜሪካ አቋም በውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ (ስቴት ዲፓርትመንት) ዋና ኃላፊ ወይም ከፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት (ኋይት ሃውስ) በኩል የሚተላለፍ እንደሚሆን ይጠበቃል። ባለፉት ሳምንታት ግማሽ ያህል የህወሃት ባለስልጣናት አሜሪካ ደርሰው መመለሳቸውን ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሌላ ዜናን ለማስተባበል ሲሞክሩ ሳያስቡት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።tplf military agazi

በሌላ ዜና በህወሃት ውስጥ “ወልቃይትን መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው” በሚሉና “ሊመለስ አይገባም” በሚል የሃሳብ ልዩነት መፈጠሩ ታውቋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው በዚሁ ጉዳይ የተሰየመው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ለቀናት ቢወያይም ስምምነት ላይ ሊደርስ ግን አልቻለም።

“ወልቃይትን እንመልስ” ባዮቹ ወገኖች አማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ አስፈሪ፣ የከረረ፣ እስከወዲያኛው ለስልጣናችን የሚያሰጋ ስለሆነ ወልቃይትን መልሶ አገሪቱን ማረጋጋት የግድ ነው ይላሉ። “ወልቃይትን መመለስ የለብንም፣ እንዴት ተደርጎስ ይመለሳል?ውርደት ነው” በሚል አቋም የያዙት ደግሞ ሁለት መከራከሪያ አላቸው።

እንደ ዘጋቢያችን መረጃ ከሆነ እነዚህ ክፍሎች ሁለት ነጥቦችን በማቅረብ የተከራከሩት “አንመልስም፣ ከመለስንም መሰረተ ልማቱንና ያፈራነውን ሃብት ምን እናደርገዋለን?” በሚል ጥያቄዎች የታጀቡ ናቸው።

“ወልቃይት የኖሩት ወገኖቻቸን ሃብት አፍርተዋል። ለማን ነው ጥለውት የሚሄዱት?” የሚሉት እነዚህ ወገኖች አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ/ሃይል በመጠቀም በተጀመረው መንገድ መቀጠል እንዳለበት የሚመኙ ሲሆኑ፣ ምኞታቸው ካልተሳካ መሰረተ ልማቱን በሙሉማፈራረስ ሌላው የመጨረሻ ውሳኔያቸው ነው።

በዚህ ሁለት ሃሳብ የሚነታረከው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዕለት ድረስ ከውሳኔ ላይ አልደረሰም። ይሁንና በዚህ ውሳኔ ላይ እንደ ከዳ የሚነገርለት ብአዴን አቋሙ እንዲጠየቅ አልተደረገም።

ህወሃት ለረጅም ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ሲያፍን የቆየው የሕዝብ ዓመጽ በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች መፈንዳቱ ሥርዓቱን ክፉኛ አናግቶታል፡፡ በፓርቲ ወይም በድርጅት ሳይመራ በሕዝብ እምቢተኝነት የገነፈለው ተቃውሞ በስልትና በግለት እየጠነከረ መምጣቱ ህወሃት የመግደል እርምጃ እንዲወስድና ከምዕራባዊ ጌቶቹ ጋር እንዲቃቃር እያደረገው ነው፡፡ በሥልጣን መቆየት በአንድ በኩል፤ በሌላ ደግሞ ከምዕራባውያን ጋር ስሙም መሆን የወጠረው ህወሃት ከዓቅሙ በላይ የሆነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ከቀን ወደ ቀን እያየለበት በንጹሃን ላይ ጥይት መተኮሱን አላቆመም፡፡

ይህ አካሄድ ህወሃትን ለክፍፍል እንደሚዳርገው ከተለያየ አቅጣጫ ይነገራል፡፡ ለዘመናት ህወሃትን ስትንከባከብ samantha powerየነበረችው አሜሪካ በተወሰነ መልኩ ጉዳዩን የማክረር ሁኔታ ይታይባታል፡፡ የአሜሪካንን ፖሊሲ የማስቀየር አቅም ያላቸው ጋዜጦች ኢትዮጵያ በአናሳዎች የምትመራ ከዴሞክራሲ የራቀች አገር መሆኗን እንደ አዲስ ለፖለቲከኞቻቸው እያስተዋወቁ ነው፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ነጻ አካል ምርመራ እንዲደረግ የተደረገውን ውሳኔ ህወሃት አልቀበልም ባለ ወቅት በመንግሥታቱ ማኅበር የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሰማንታ ፓወር ህወሃት “ነጻ ምርመራውን መቀበል አለበት” በማለት በትዊተር የከረረ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

መጪው ጊዜ የከፋ እንደሚሆን የገመቱ፣ ለዘብተኛ ለመሆን የሚፈልጉና በሃብት የደለቡ የህወሃት ሰዎችና አሽከሮቻቸው “በጥገናዊ ለውጥ” ሁኔታዎች እንዲረግቡ ይፈልጋሉ፡፡ ምዕራባዊ አገራት በመቆየት ዘምነናል የሚሉና የምዕራባውያን ድጋፍ እንዳላቸው በተለያየ መልኩ የሚጠቅሱት በዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ህወሃት/ኢህአዴግ ከየቦታው የሰበሰባቸውና በየአገሩ ተወካይ (አምባሳደር) አድርጎ ያስቀመጣቸው ተላላኪዎቹም ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ክፍሎች በራሱ በህወሃት ከረከሰው ሽምግልና እስከ ዕርቅ ለመሄድ የሚጥሩትንም ይጨምራል፡፡ ብንከስርም ወልቃይትን ለባለቤቱ እንመልስ ባዮቹ የዚህ ዓላማ አራማጆች ናቸው፡፡ የነዚህ ተቃራኒዎች ማሸበርና መግደል በመቀጠል “ካልገዛን እንሞታለን” ብለው ህወሃትን ከጌቶቹ ከማቃቃር እስከ “አሜሪካ ከከፋት ጉዞ ወደ ቻይና” የሚሉ የተሰባሰቡበት ነው፡፡ የበረሃ ገድላቸውን እየጠቀሱ “ደጋፊዎቻቸው” ጠብመንጃ እንዲወለውሉ የሚቀሰቅሱና “ሪፓብሊካቸውን” በአየር ኃይል ጭምር ለመከላከል የወሰኑ በዚህ ምድብ ውስጥ ተከማችተዋል፡፡

የእነዚህና ሌሎች ኃይላት ትንቅንቅ ህወሃትን አደገኛ ፈተና ውስጥ እንደጣለው ይነገራል፡፡ አራት ዓመታት በሙት መንፈስና ሌጋሲ ሲመራ የቆየው ህወሃት/ኢህአዴግ ታዛዥነት፣ መደማመጥና “ብልጠት” ጠፍቶበት “ባለ ራዕይ መሪውን” ክፉኛ ናፍቋል፡፡

Received on Thu Aug 18 2016 - 09:58:17 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved