Ethsat.com: የጢስ አባይ ነዋሪዎች እና ወታደሮች ሲታኮሱ ዋሉ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Wed, 10 Aug 2016 00:24:37 +0200

የጢስ አባይ ነዋሪዎች እና ወታደሮች ሲታኮሱ ዋሉ

August 9, 2016

Watch these:

http://video.ethsat.com/?p=26889

http://video.ethsat.com/?p=26911

ESAT People’s Voice August 09 , 2016 Ethiopia

1. http://video.ethsat.com/?p=26894

2. http://video.ethsat.com/?p=26903

ነሃሴ  ፫ ( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር በተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ የተገደለውን አንድ  የጢስ አባይ ተወላጅ ደም ለመበቀል የሟች ቤተዘመዶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ሌሊቱን ከአጋዚ ጦር ጋር ጠበንጃ አንስተው ሲዋጉ ማደራቸው ከጢስ አባይ የወጡ መረጃዎች የክልዩ ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡በጢስ አባይ ከተማ ያለው ውጥረት እየተባባሰ በመሄዱ ዛሬ ረፋዱ ላይ  ከአንድ መቶ ሃያ በላይ ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት  ከተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች በአንቶኖቭ በመምጣት ወደ ጪስ አባይ ለውጊያ ተልኳል፡፡ የአካባቢው ታጣቂም ፍልሚያውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

ጢስ አባይ ከባህርዳር በቅርብ እርቀት ላይ የምትገኝ የአባይ ፏፏቴ የሚገኝባት መለስተኛ ከተማ ናት።

በተመሳሳይ ዜና የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ወደ ሰሜን ጎንደር ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በመጓዝ ህዝቡ ተቃውሞ እንዳያነሳ በሃይማኖት አባቶች በኩል ለማስገዘት እና አመራሩን እና ህዝቡን ለማስታረቅ ያደረጉት ሙከራ በአብዛኛው ሳይሳካ ቀርቷል።

በጎንደር ሲኒማ አዳራሽ የአብዴኑ በረከት ስምኦን የኢህአዴግ ደጋፊዎችን ብቻ በመጥራት ስብሰባ ለማድረግ መሞከሩ ሲሰማ ወጣቱ በብዛት ወደ አዳራሹ በመግባቱና ጠንካራ ጥያቄዎችን መጠየቅ በመጀመሩ፣ አቶ በረከት በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነን ስብሰባ ለማድረግ ስለማንችል ስብሰባው ተበትኗል ብሎ ስብሰባው እንዲበተን ካደረገ በሁዋላ፣ ወጣቶቹ በቁጣ አዳራሹን በድንጋይ የደበደቡ ሲሆን፣ አቶ በረከትም በወታደሮች ታጅቦ ወጥቷል። ወጣቱ ተቃውሞውን በሚቀጥልበት ወቅት በከተማው በብዛት የሚገኙት ወታደሮች አስለቃሽ ጭስ በመበተን ለመቆጣጠር ሙከራ አድርገዋል።

ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ ነገ ረቡዕ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ትበሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የጎንደር ነዋሪዎችም በቦታው ተግኝተው ተቃውሞ እንደሚያሰሙ እየተናገሩ ነው።

በሳንጃ ከተማ ደግሞ የብአዴን ባለስልጣናት የሃይማኖት አባቶችን በመያዝ የስርዓቱን ወታደሮች እና አርሶደሮችን ለማስታረቅ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን፣ አርሶአደሮች ወታደሩ ድንበር መጠበቅ ሲገባው የገዛ ህዝቡን እንዴት ይጨፈጭፋል በማለት በቁጣ ሲናገሩ ውለዋል።

በተለያዩ የአማራ ከተሞች በሳምንቱ መጨረሻ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች የተጀመሩ ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲ በርካታ የመከላከያ ሰራዊቱን በየከተሞች እየወሰደ በማስፈር ላይ ነው። የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጸው  ወጣቶች ወታደሮችን ከምንም ባለመቁጠር በሰልፉ ላይ ለመገኘት ዝግጀቶችን እያደረጉ ነው። ተቃውሞውን ሊመሩ ይችላሉ የተባሉ ወጣቶች እየተመረጡ በመታሰር ላይ መሆናቸውም ታውቋል።

በኦሮምያ ክልል ደግሞ ፖሊሶች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ  ላገለገሉበት የ ስራ የውሎ አበል በሚል እስከ 500 ብር በነፍስ ወከፍ ተከፍሎአቸዋል። የአዲስ አበባ ፖሊሶች በተቀራኒው ወደ ባህርዳር ሄደው ስራ እንዲሰሩ ሲጠየቁ፣ ደሞዝ የጨመራችሁለት አካል ይሂድ እኛ አንሄድም ብለው መቃወማቸውን ምንጮች ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ፖሊሶች አድማ የመበተን ልምድ አላቸው በሚል ወደ ባህርዳር ሂደው በከተማው የተነሳውን ህዝባዊ ንቅናቄ እንዲያበርዱ በገዢው ፓርቲ በኩል ፍላጎት እንደነበር ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

*****************************************************************************************

በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የጅምላ አፈሳ እየተካሄደ ነው ተባለ

August 9, 2016

ኢሳት (ነሃሴ 3 ፥ 2008)

በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች በመካሄድ ላይ የለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በአካባቢው የጅምላ አፈሳ በመካሄድ ላይ መሆኑን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ።

የክልሉ ፖሊስና የደህንነት ሃይሎች ጨለማን ተገን በማድረግ ተቃውሞን አስተባብረዋል ብለው የጠረጠሯቸውን አካላት በማሰር ላይ እንደሆኑ ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ከዜና ክፍላችን ጋር በደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል።

በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢው ሰፍረው የሚገኙ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡና ለሚጠሩ ስብሰባዎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት የጸጥታ ሃይሎች እርምጃን በመውሰድ ላይ እንደሆኑ ከነዋሪዎቹ ለመረዳት ተችሏል።

አቶ በረከት ስምዖንን ጨምሮ የተለያዩ የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) አመራሮች ከነዋሪዎች ጋር ውይይትን ለማካሄድ ቢሞክሩም በነዋሪዎች ተቃውሞ ምክንያት ውይይቱ መጨናገፉን እማኞች አስረድተዋል።

በአመራሮቹና ነዋሪዎቹ መካከል ሊካሄድ የታሰበው ውይይት መጨናገፉን ተከትሎ የጸጥታ ሃይሎች መጠነ ሰፊ የጅምላ እስራት በማካሄድ ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በአካባቢው የሚገኙ የክልሉ ፖሊስ አባላትና ሚሊሺያዎች ነዋሪው በተለይ ወጣቱ ራሱን በማደራጀት እንዲንቀሳቀስ ጥሪ ማስተላለፋቸውን እማኞች አክለው አስታውቀዋል።

የሃይማኖች አባቶችን ጨምሮ የዞንና የወረዳ ባለስልጣናት በጎንደር እና ባህርዳር ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች የዕለት ከእለት የኑሮ እንቅስቃሴያቸውን እንዲቀጥሉ ሰኞ ጥረት መጀመራቸው ይታወሳል።

ይሁንና በሁለቱ ከተሞችና በዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እየቀረበላቸው ያለን ጥሪ ባለመቀበል ስራ አለመጀመራቸውን እማኞች ለኢሳት አስረድተዋል።

በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ተቃውሞን እያካሄዱ ያሉ ነዋሪዎች ለእስር የተዳረጉ ሰዎች እንዲፈቱና ግድያና እስራት እንዲቆም እንዲሁም የሰብዓዊ መብት እንዲከበር ጥያቄን እያቀረቡ ይገኛል።

Received on Tue Aug 09 2016 - 17:03:42 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved