Ethsat.com፡ የጎንደር ህዝብ ከእንግዲህ በህወሃት /ኢህአዴግ አንገዛም አለ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sun, 7 Aug 2016 23:49:21 +0200

የጎንደር ህዝብ ከእንግዲህ በህወሃት /ኢህአዴግ አንገዛም አለ

ነሓሰ 7, 2016
Watch these:

ESAT People’s Voice From Bahir Dar and Other Places Part 1 August 07 , 2016

http://video.ethsat.com/?p=26787

ESAT People’s Voice From Bahir Dar and Other Places Part 2 August 07 , 2016

ሐምሌ  ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጎንደር ከተማ ህዝብ ገንፍሎ በመውጣት በህዋሀት ኢህአዴግ ላይ ያለውን ተቃውሞ ሲያሰማ ውሎአል። ከእየቦታው የተሰባሰበው የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ በቀጥታ በመተኮስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። በአዘዞ በአርሶአደር ታጣቂዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። የህዝቡን ትግል ለመርዳት ከወልቃይትና ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ታጣቂዎች ወደ ጎንደር መግባታቸውን ተከትሎ ወታደሮቹ ጥቃታቸውን ቀንሰዋል። በልዩ ሃይል እና በመከላከያ መካከል ልዩነት መፈጠሩንም የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ምንም እንኳ እስካሁን የሞቱ ሰዎችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ ባይቻልም፣ በአዘዞና በጎንደር በአጠቃላይ ከ7 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። ከተገደሉት መካከል 2ቱ ሴቶች ናቸው። በጎንደርም  ከገዢው ፓርቲ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የተለያዩ የንግድ መደብሮች ወድመዋል። በአዘዞ ደግሞ ፖሊስ ጣቢያውና አንድ ሆቴል ተቃጥሎአል። የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋምም  ተሰባብሯል። የዳሽን ቢራ አርማን የሰቀሉ ሆቴሎች አርማቸው እንዲወርድ ተደርጎ ተቀዳዷል።

ከሰአት በሁዋላ ደግሞ ገዢው ፓርቲ የኢንተርኔት እና የፌስ ቡክ አገልግሎት እንዲቋረጥ አድርጓል። የስልክ መስመር ግንኙነቱንም አስቸጋሪ አድርጎታል። የጎንደር ህዝብ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል።

በመላ አገሪቱ ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ሲሆን፣ በነገው እለት በመላ ኦሮምያ የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ለማኮላሸት የጸጥታ ሃይሎች በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች እየተገኙ ህዝቡን ለማስፈራራት እየሞከሩ ነው። አዲስ አበባንና አዳማን ጨምሮ በሚካሄደው ተቃውሞ መላው ህዝብ ተገኝቶ በኦሮምያ እና በጎንደር እየደረሰ ያለውን ጨፍጨፋ ያወግዛል ተብሎ ይጠበቃል።

በባህርዳርና በደብረታቦርም እንዲሁ እሁድ የተቃውሞ ሰልፎች ያከሄዳሉ። የተቃውሞ ሰልፉን የተሳካ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች የተጀመሩ ሲሆን፣ በተለይ በደቡብ ጎንደር መፈክሮች እየተጻፉ ተበትነዋል።

በጎንደር ተቃውሞው የተጀመረው የኮ/ል ደመቀ ዘውዴን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተከትሎ ሲሆን፣ ህዝቡ ኮሎኔሉ ፍርድ ቤት አለመቀርባቸውን በማዬት ተቃውሞውን ጀምሯል። በፍርድ ቤት ውስጥ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ ወጣቶቹ ፍርድ ቤት ላይ የነበረውን ባለኮከቡን ሰንደቃላማ በማውረድ ኮከብ ባለው ሰንደቃላማ ተክተዋል። በፒያሳም እንዲሁም በመንገዶች ላይ የነበሩ ሰንደቃላማዎች ወርደው አርማ በሌለው ተተክተዋል።

የጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የኮሎኔል ደመቀን ጉዳይ አንይዝም ማለት የጀመሩ ሲሆን፣ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ባህሩ አዲስ ግን ህዝቡን ዝም ካሰኛችሁት ክሱን አያለሁ ማለታቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ዳኞች ለኢሳት ተናግረዋል።

Received on Sun Aug 07 2016 - 16:28:25 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved