Zehabesha.com: ከጎንደር ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ማክሰኝት ድረስ ዐማራው ተጋድሎውን አጠናክሮ ቀጥሏል- ሙሉቀን ተስፋው

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sat, 6 Aug 2016 00:26:05 +0200

ከጎንደር ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ማክሰኝት ድረስ ዐማራው ተጋድሎውን አጠናክሮ ቀጥሏል- ሙሉቀን ተስፋው

ተመልከተው፡

http://video.ethsat.com/?p=26667

gonderከጎንደር ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ማክሰኝት ድረስ ዐማራው ተጋድሎውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በማክሰኝት ከተማ ዐማሮች ገንፍለው ወጥተው በምሽት ተጋድሏውን ቀጥለዋል፡፡ የመለስ ፎቶን የያዘ ቢል ቦርድ ተቃጥሏል፡፡ ወደ ጎንደር ለእርዳታ እየፈጠኑ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ሆኖም በጎንደር የወያኔ ጦር ከንጹሐን ዐማሮች ላይ የለየለትን ጦርነት ካወጀ ከሰአታት በኋላ ስልክና ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ተቋርጧል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ስልክ የሚሠራ የነበረ ቢሆንም አሁን ሙሉ በሙሉ ከመረጃ ምንጮቻችን ጋር ግንኙነታችን ተቋርጧል፡፡ ይህን መልእክት የሚያነብ የዐማራ ሕዝብ እልቂት የሚያሳስበው ወገን ሁሉ በውስጥ መስመር የሚያገኘውን መረጃ እንዲያቀብል በዚሁ አጋጣሚ እንጠይቃለን፡፡ ከአርማጭሆና ከቋራ አካባቢ ወገኖቻቸውን የሚታደጉ ዜጎች እየመጡ መሆናቸውን ብንሰማም ወደ ከተማ ስለመግባታቸው ግን የታወቀ ነገር የለም፡፡

Received on Fri Aug 05 2016 - 17:05:10 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved