Mereja.com: ሕወሓት በአወዳይ በወሰደው እርምጃ 6 ንጹሃን ተገደሉ ከ26 በላይ ቆሰሉ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Mon, 1 Aug 2016 20:18:06 +0200
ሕወሓት በአወዳይ በወሰደው እርምጃ 6 ንጹሃን ተገደሉ ከ26 በላይ ቆሰሉ


በዛሬው እለትም የቤት ለቤት አፈሳው ቀጥሎ ውሏል የትልቁን መስጅድ ኢማም ከመኖሪያ ቤታቸው እየደበደቡ እንደወሰድዋቸውእማኞች ለቢቢኤን ገልጸዋል:: በበዴሳ በተደረገው ተቃውሞ ህዝቡ እስር ቤትን በመስበር እስረኞችን አስፈትቷል።

በትላንትናው እለት የመንግስት አጋዚ ወታደሮች በከፈቱት ጥቃት 6 ሲገደሉ 26 በላይ እንደቆሉ ታውቋል፡፡ በዛሬው እለት በከተማዋ ማወከቡ መቀጠሉን የገለጹት ምንጮቻችን በዛሬው እለትም በየቤቱ ወንዶችን እያሰሩ እንደነበር ገልጸዋል ፡፡ ሸህ አህመድ አሊሾ የተባሉትን የአወዳይ ትልቁን መስጅድ ኢማም ከቤታቸው እየደበደቡ እንደወሰዱዋቸው የቢቢኤን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በዴሳ በተደረገው ተቃውሞ ህዝቡ እስር ቤትን በመስበር እስረኞችን አስፈትቷዋል።
የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች በወሰዱት የሀይል እርምጃ 4 ሰው በጠይት የተመታ ሲሆን አንዱ ወዲያው ሞቶዋል።

 
 
Received on Mon Aug 01 2016 - 12:57:11 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved