Goolgule.com: ብአዴን እንደ ኦህዴድ ከዳ?! ሕዝብ አለ! አደረገ!

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Mon, 1 Aug 2016 18:02:14 +0200

ብአዴን እንደ ኦህዴድ ከዳ?!

ሕዝብ አለ! አደረገ!
gondar18
 

በጎንደር ከተማ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ ሰላማዊ ትዕይንተ ሕዝብ አካሄደ፡፡ አገራዊና ሕዝባዊ ጥያቄዎችን በማቅረብ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሚካሄደው ትግል ያለውን ድጋፍ ገለጸ፡፡ ስልታዊ ጥርነፋውን አልፎ ትዕይንተ ህዝብ ለማድረግ መቻሉ ብአዴን ህወሃት የሚዘውረውን ኢህአዴግ ለመክዳቱ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡

እሁድ ሐምሌ 24፤2008ዓም በጎንደር ከተማ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ህወሃት/ኢህአዴግ ገና ከጅምሩ የማምከን ተግባር ለመፈጸም በርካታ የጸጥታ አባላትን በስፍራው መድቦ ነበር፡፡ ሆኖም ሕዝብ ከቀናት በፊት በተናገረው እና ራሱ ኢህአዴግ እመራበታለሁ በሚለው ሕገመንግሥት መሠረት ሰላማዊ ሰልፉን አስቀድሞ አሳውቆ፤ በአግባቡ መልዕክቱን አስተላልፎ በክብር ተመልሷል፡፡ ዓላማውን የሚያውቅና ለሚያምንበት የቆመ ህዝብ እስካለ ድረስ ኢህአዴግ ሰልፍ ቢፈቅድም ባይፈቅድም ሕዝብ ያለውን ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በማሳየት ለመማር ለሚፈልጉ ትምህርት ሰጥቶ አልፏል፡፡

ህወሃት ሰልፈኞቹ በአማራነት የጎሣ አስተሳሰብ ብቻ ጠብበው እንዲወጡ በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካለትም፡፡ የትግራይ ሕዝብ ላይ ጥላቻ የሚቀባ ተግባር እንዲፈጸምና ይህንንም ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ያሰበው ህወሃት “የሻዕቢያ ተላላኪ ራሱ ህወሃት እንጂ ወልቃይት አይደለም” በሚል መፈክር ምላሽ ተሰጥቶታል፡፡ ችግሩ ያለው ከህወሃት ጋር እንጂ ከትግራይ ህዝብ ጋር እንዳልሆነ ሰልፈኛው በማያሻማ መልኩ ግልጽ ማድረጉ ስርዓቱን እንደግፋለን ለሚሉ የትግራይ ተወላጆችና አክራሪ ወያኔዎች ከጅምላ አስተሳሰባቸው ወጥተው ምላሽ እንዲሰጡ ያስገደደ ሆኗል፡፡ የሰልፈኛው ብዛትና የተቃውሞው ብርታት መቶ በመቶ አሸንፌአለሁ ለሚለው ኢህአዴግ በዓለምአቀፍ ኅብረተሰብ ዘንድ ጥሩ የቤት ሥራ ሰጥቶ አልፏል፡፡gondar7

በዚህ ህዝብንና የፖለቲካ አስተሳሰብን ለይቶ ተቃውሞውን በግልጽ ባሰማ ትዕይንተ ህዝብ ላይ ለ25ዓመታት ሲደሰኮር የኖረው የህወሃት የሠንደቅ ዓላማ ጉዳይ በግልጽ ምላሽ አግኝቷል፡፡ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ብቻ አሁንም የኢትዮጵያ መለያ ሰንደቅ መሆኑን ሰልፈኞቹ በይፋ አሳይተዋል፡፡ ባለሰማያዊ ኮከቡን ባንዲራ ይዞ ያልወጡ ሕገመንግሥት ለመናድ የሞከሩ እየተባሉ ሲታሰሩ፣ ሲሰቃዩ፣ … በቆዩባት ህወሃት በግፍ የሚገዛት ኢትዮጵያ ኮከብ አልባውን ሠንደቅ አገር ውስጥ ከፍ ብሎ ሲውለበለብ ማየት የሥርዓቱን ክስረት በግልጽ ያሳየ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህም ሌላ ሰልፈኞቹ “በኦሮሚያ የሚደረገው የወንድሞቻችን ግድያ ይቁም፤ በጎዳና ላይ የሚፈሰው የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን ደም የእኛም ደም ነው” የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት፤ በእጃቸውም ምልክት በማሳየት ወራትን ላስቆጠረው የኦሮሞ ትግል ያላቸውን ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡ ይህም የኦሮሞን ትግል እንመራለን ለሚሉ ትልቅ ተግዳሮት የጣለ ሆኗ አልፏል፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ችግር ፈጣሪ ህወሃት እንደመሆኑ ከጎንደር ለታየው ግልጽ የወገናዊነት ድጋፍና አጋርነት በኦሮሞ አካባቢዎችም እንዲታይ መመሪያ ይሰጡበታል ወይስ “የኦሮሞ ህዝብ ያለማንም አጋዥነት ራሱን ነጻ ያወጣል” በሚል ጭፍን አስተሳሰብ የህወሃትን የዘር ፖለቲካ ሳያውቁት እየደገፉ ይቀጥላሉ? ይህ በቀጣይ ግልጽ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡gondar bekele

በዚህ ትዕይንተ ሕዝብ ህወሃት በየቦታው ያቋቋመው የአምስት ለአንድና ሌሎች የመጠርነፊያ ስልቶች ዋጋቢስ እየሆኑ መሄዳቸው በግልጽ ታይቷል፡፡ የኦህዴድ የበታችና የመካከለኛ አመራሮችና ካድሬዎች ለህወሃት አንገዛም በማለታቸው በርካታ ተቃውሞዎች በኦሮሚያ ሊካሄዱ የመቻላቸውን ያህል በጎንደርም እንዲሁ በህወሃት የተዘረጋውን ጥርነፋ የብአዴን አመራሮች ከማላላት አልፈው ውስጥ ውስጡን መደገፋቸው ከዚህ ትዕይንተ ህዝብ ጋር በተያያዥ የሚጠቀስ ነው፡፡ ሁልጊዜ ሁለተኛነትን ቦታ በደስታ ሲጫወት የኖረው ብአዴን በዚህ መልኩ እየከዳ ከሄደ እና ከኦህዴድ ጋር ግልጽ አጋርነት ከፈጠረ ህወሃት በኢህአዴግ ስም ደኢህዴንን ብቻ እየዘወረ የትም እንደማይደርስ በተደጋጋሚ ሲነገር የኖረ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የትግል አጋርነት ማሳየትና ባለራዕይ መሆን እንደሚያስፈልግ አገራዊ አጀንዳ በሚያራምዱ ዘንድ በግልጽ ይነገራል፡፡

ፕ/ር መስፍን ፌስቡክ ገጻቸው ላይ በእንግሊዝኛ ባሰፈሩት ሃሳብ “ሕጋዊ ጥያቄዎች ህጋዊ ምላሽ ይሻሉ” ካሉ በኋላ “ይህ ፖለቲካ ነው፤ ሕገ አራዊት መወገድ አለበት፤ ጀማሪና ብቃት ያጠራቸው ሹሞች ወደአእምሯቸው ተመልሰው በአገሪቷ ላይ ያለው አደጋ እጅግ አደገኛ መሆኑን ሊያስተውሉ ይገባል” ብለዋል፡፡

“ሁላችንም ለእያንዳንዳችን፤ እንዳንዳችን ለሁላችንም፤ ስንተባበር እንቆማለን፤ ስንከፋፈል እንወድቃለን” በማለት “የኦሮሞ ደም የለም፤ የአማራ ደም የለም፤ … ሁላችንም የአንድ ደም ውጤቶች ነን፤ ከዘር በፊት ሰብዓዊ ፍጡራን ነን” በማለት የሚታወቁት አቶ ኦባንግ ሜቶ ከጎንደሩ ትዕይንት ጋር የተያያዘ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳሬክተር የሆኑት ኦባንግ በዚህ መልዕክታቸው ላይ “የተባበረ ህዝብ መቼም ቢሆን አይወድቅም፤ ሕዝባችን እንደ አንድ ቤተሰብ በአንድነት ሲቆም መመልከት የሁላችንም የምትሆነውን አዲሲቷን ኢትዮጵያን ለመመሥረት የሚያስችለን በመሆኑ ተስፋና መጽናናት ይሰጠኛል፤ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ በሆነው ሠንደቅ ዓላማ ስር በኩራት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ መመልከት ታላቅ ደስታ ይሰጠኛል” ብለዋል፡፡ አቶ ኦባንግ በዚህ መልዕክታቸው የችግራችን ምንጭ አንድ በመሆኑ በአፓርታይዳዊ ስልት የዘር መከፋፈል ያመጣብንን የህወሃት ሥርዓት በአንድነት መታገል እንደሚገባ ሁሉንም የኢትዮጵያ ወገኖች በማሳሰብ ተባብረን ከቆምን ፍትህ በኢትዮጵያ የሚሰፍንበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡gondar9

በትዕይንተ ህዝቡ ላይ ከተሰሙት መፈክሮች ጥቂቶቹ፡-

የሻዕቢያ ተላላኪ ህወሃት እንጂ ወልቃይት አይደለም!

በኦሮሚያ የሚካሄደው የወንድሞቻችን ግድያ ይቁም!

አገራችንን ለሱዳን አሳልፈን አንሰጥም!

መብታችን ይከበር!

ለሱዳን የተሰጠው የሱዳን መሬት በአስቸኳይ ይመለስ!

በጋምቤላ የሚካሄደው አፈና በአስቸኳይ ይቁም!

ኮሎኔል ደመቀ በአስቸኳይ ይፈታ!

የወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ እንደሆነ እናረጋግጣለን!

በጎዳና ላይ የሚፈሰው የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን ደም የእኛም ደም ነው!!

የሚሉና ሌሎችም ይገኙባቸዋል፡፡ (ፎቶዎቹን ያሰባሰብነው ከማኅበራዊ ገጾች ነው)

gondar1

gondar3

gondar2

gondar4

gondar9

gondar6

gondar7

gondar8

gondar10

gondar11

gondar19

gondar16

gondar25

gondar23

gondarsebhat

gondar25

ሌሎች ፎቶዎችንና ባለፉት 24 ሰአታት በኦሮሚያ እየተካሄደው ስላለው ተቃውሞ ግርማ ሞገስ የላኩልንን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

Received on Mon Aug 01 2016 - 10:41:19 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved