ESAT News: Security forces open fire at protesters in Borena, three sustain injuries

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 29 Jul 2016 00:47:05 +0200

Security forces open fire at protesters in Borena, three sustain injuries

Screenshot_2016-07-28-00-46-13

Photo: social media

July 28, 2016

ESAT News

http://video.ethsat.com/?p=26357

http://video.ethsat.com/?p=26372

Security forces opened fire at residents in Borena, south Ethiopia as they try to quell ongoing protest demanding an end to tyranny.

Several security officers entered the town of Kulubuma in Borena after protests against the regime reignited on Tuesday demanding an end to years of oppression against a tyrannical regime.

Security forces opened fire at a gathering of people who were not even staging protests, injuring three including a visitor to the town and a woman who work as a street vendor.

The protest by the people in the Oromo region against years of economic and political marginalization has been going on for eight months now and resumed last week after a lull for few weeks.

Over 400 people were killed and thousands of others injured as security forces use deadly force against protesters. Tens of thousands remain in detention.

*****************************************************************************************

በጎንደር ለእሁድ የተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ እንደማይታጠፍ ነዋሪዎች አስታወቁ

July 28, 2016

ሐምሌ  ፳፩ ( ሀያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጋር በተያያዘ በሰሜን ጎንደር የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ  ለማብረድ ገዢው ፓርቲ የተለያዩ የማዘናጊያ ስልቶችን ቢጠቀምም፣ በህዝቡ ውስጥ ያለው ስሜት ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ማለቱን ዛሬ በጎንደር   መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን የተሰበሰቡት የኮሚቴ አባላትና በስብሰባው ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። በመጪው እሁድ  ሃምሌ 24፣ 2016 ከጠዋቱ 2 ሰአት ጀምሮ የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ተፈቀደ አልተፈቀደ ሰልፉን ከማድረግ ወደ ሁዋላ የሚያግዳቸው ነገር እንደሌለ ወጣቶች ተናግረዋል።

በስብሰባው ላይ ከ300 በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል። የጎንደር ዩኒቨርስቲ አመራር የመኪና አገልግሎት በመስጠት ችግር እየፈጠረ መሆኑን ተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። ደህንነቶች ሆን ብለው ሽፋን ለማግኘት የዩኒቨርስቲውን መኪኖችና አምቡላንሶች ሳይቀር እየተጠቀሙ ነዋሪዎችን እየሰለሉ በመሆኑ፣ የዩኒቨርስቲው አመራሮች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።

ትናንት በከንቲባው ጽ/ቤት አቶ በረከት ነዋሪዎችን ሰብስበው በነበሩበት ወቅት “ ሰላማዊ ሰልፉን ሰላማዊ በሆነ መልኩ እስካካሄዳችሁ ድረስ ችግር የለም” ብለው ቢናገሩም፣ ዛሬ ግን ስብሰባውን ማካሄድ አይቻልም የሚል ትእዛዝ ለኮሚቴው አባላት መተላለፉ ታውቋል። አቶ በረከት “ የድንበሩን ጉዳይ ለመፍታት 3 ወር ይወስዳል፣ የማንነትን ጥያቄ በተመለከተ ግን ስብሰባውን በሰላም ማካሄድ ትችላለችሁ” ብለው ማናገራቸውን ተሰብሳቢዎች ተናግረዋል።

የኢህአዴግ አመራሮች የተለያዩ አወዛጋቢ መልሶችን መስጠታቸው ወጣቶችን ያስቆጣ ሲሆን፣ አመራሮቹ ምንም ይበሉ   የእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ የሞት ቀጠሮ ነው ብለዋል።

“ከእንግዲህ የደህንነት ሃይሉና ወታደሩ  እጃችንን ሊይዝ ቢሞክር ሁላችንም  የኮሎኔል ደመቀን መንገድ እንደምንከተል እናሳያቸዋለን ሲሉ ወጣቶች ተናግረዋል።

በሰልፉ ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ የሰሜን እና የደቡብ ጎንደር ከተሞች ነዋሪዎች ወደ ጎንደር ከተማ እየተጓዙ ነው። ይህን እንቅስቃሴ ለመግታት በባህርዳር፣ ደሴና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች ጥብቅ ፍተሻ በመደረግ ላይ ነው።

በነገው እለት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ጎንደር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። ህዝቡ ወደ ፍርድ ቤት በማምራት ለኮሎኔሉ ያለውን ድጋፍ ይገልጻል ተብሎ የጠበቃል።

በክልሉ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ወደ ጎንደር ጉዞ ለሚያደርጉ የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች ተቢውን የተሽከርካሪ አገልግሎት እንዲሰጡም ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

ህዝቡ በሰልፉ ላይ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ እንዲመለስ፣ የታሰሩት በሙሉ እንዲለቀቁ፣ ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ ከእገታ እንዲወጣ እንዲሁም በዘር ላይ የተመሰረተው የህወሃት አገዛዝ እንዲያበቃ ይጠይቃል ተብሎ ይጠበቃል። ጋጠወጥ በሆነ መልኩ የህዝቡን የነጻነት ትግል ያራከሱት የኮሚኬሽን ሚኒስቴር ጌታቸው ረዳ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ እንዲሁም ሬዲዮ ፋና የጎንደርን ህዝብ በይፋ በመገናኛ ብዙሃናቸው ይቅርታ መጠየቅ እንዳለባቸው የጎንደር ህዝብ እያሳሰበ ነው።

ሀምሌ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ በነበረው አመጽ፣ 18  ወታደሮች መገደላቸውን ባህርዳር በነበረው የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስብሰባ ላይ ተነስቶ ነበር። እነዚህ የሰራዊት አባላት በህዝባቸው ላይ ለመተኮስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ የአጋዚ ሰራዊት አባላትን በማሰማራት ጥበቃ በማድረግ ላይ  ነው።

Received on Thu Jul 28 2016 - 17:26:10 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved