Zehabesha.com: በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ያለው ጉምጉምታ ወደ ተግባራዊ ፍጥጫ እያመራ መሆኑ ተሰማ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sat, 23 Jul 2016 01:00:07 +0200

በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ያለው ጉምጉምታ ወደ ተግባራዊ ፍጥጫ እያመራ መሆኑ ተሰማ

solder ethiopian

solder
ከልዑል ዓለሜ

በህወሃት በህወሃት የመከላከያ ፖለቲካ መምሪያ እና የፕሮፓጋንዳ ክፍሎች ምንጭ እንደሚያመለክተዉ በሰሞኑ ጎንደር ላይ የተገደሉትን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ትዉልድ ቦታቸዉ ተወስደዉ በክብር መቀበራቸዉ ተንተርሶ በሰራዊቱ ዉስጥ ቅራኔ ተፈጥሯል:: ይህዉም:-
1. ከሟቾች ዉስጥ ትግሬ የሆኑ አባላት ስላሉበት ነዉ የቀብሩ ስነ ስርአት በክብር የተከናወነዉ::


2. ዉስጥ ዉስጡን የሚሰራ የብሔር ማናከሱ ደባ በአማራ የተገደሉ ትግሬዎች ናቸዉና ትግሬ የሆንክ ሁሉ ለዘላቂ መኖርህ ሕልዉና ስትል ከህወሃት ጋር እስከ ሞት ድረስ ቁም የሚል የጽንፍ መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ ነዉ።

የሚሉ ሲሆን ሰራዊቱ በሶማሌያ፣ በኤርትራ፣ በኦጋዴን፣ በአፋር፣ በጋንቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በተለያዩ የድንበር አካባቢዎች ሲገደሉ ወይም ሲሰዉ የመከላከያ አባላቶቹ ከነመፈጠራቸዉም ስማቸዉ ተነስቶ አይታወቅም።

ይህ ለምንና እንዴት እንደሆነ ባለስልጣናት የሆኑ የህወሃት አመራሮች ሲጠየቁ ህወሃት ከጅምሩ ወታደሮችን በሞቱበት ስፍራ የመቅበር ባሕል አላት ብለዉ ይቀልዳሉ በማለት ማጉረምረሙ ወደ ቅራኔ እየተቀየረ መምጣቱን ለመረዳት ምንጮች ጠቁመዋል።

በተያያዘ ዜና በአሁኑ ወቅት በጎንደር የተከሰተዉን የህዝብ መከላከል ተንተርሶ ህወሃት ከፍተኛ ስጋት ላይ የወደቀ ሲሆን በተጨማሪ በዚህ ሁለት ቀናት ዉስጥ በጎረቤት ሐገር ድንበር አካባቢ የህወሃት 24ተኛ ክ/ጦር ድንገተኛ ጥቃት ደርሶበታል።

Received on Fri Jul 22 2016 - 17:39:12 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved