Zehabesha.com: ኢንስፔክተር ተስፉ የተሰኘ የፌደራል ፖሊስ ጦር መሪ በርካታ አባላትን ከነሙሉ ትጥቃቸው ይዞ ከሁመራ ስርዓቱን ከዳ፡፡

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Mon, 29 Feb 2016 00:05:43 +0100

February 28, 2016

ኢንስፔክተር ተስፉ ሁመራ እና አካባቢው የሚንቀሳቀሰው ፌደራል ፖሊስ መሪ፣ ለህወሓት ታማኝ እና ጠንካራ ከሚባሉት ቀዳሚው የነበረ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የካቲት 19 2008 ዓ.ም የሚመራቸውን በርካታ አባላት ከነሙሉ ትጠቃቸው ይዞ ሁመራ ከሚገኝ ጦር ግንባር ጠፍቷል፡፡

የኢንስፔክተር ተስፉን እና በርካታ ተከታዮቹ የሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላትን መጥፋት ተከትሎ ህወሓት ጎዳናዎችን በጦር ዘግቶ ወጥሯል፤ ከፍተኛ አሰሳም እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ኢንስፔክተር ተስፉና ተከታዮቹ እስካሁን የገቡበት አልታወቀም፡፡ አገዛዙ እነ ኢንስፔክተር ተስፉ ወደ ኤርትራ ተሻግረው ብረት ያነሱ የነፃነት ድርጅቶችን እንደተቀላቀሉ ያምናል፡፡

 
Received on Sun Feb 28 2016 - 18:05:43 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved