Zehabesha.com: 1. በአምቦ እስር ቤት ተቃጠለ | ከተማዋ በጥይት ድምጽ ተወጥራለች 2. በአደባባይ ተሰቅሎ ዓመታት ያስቆጠረው የመለስ ዜናዊ ፎቶን የያዘው ትልቅ ፖስተር በዶዶላ ተቃጠለ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 19 Feb 2016 21:08:54 +0100
http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/02/ambo.jpg

(ዘ-ሐበሻ) በአምቦ ከፍተኛው ተቃውሞ በቀጠለበት በዚህ ወቅት በከተማዋ የሚገኘው እስር ቤት በ እሳት እየነደደ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

በተለምዶው ቀበሌ 06 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ይኸው የፖለቲካ እስረኞች ማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ ከኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ ጋር በተያያዘ የታሰሩ በርካታ ወገኖች እንደደሚገኙበት ምንጮች አስታወቀዋል::

በአምቦ ከተማ በአሁኑ ወቅት የጥይት እሩምታ እየተሰማ ሲሆን ከዚህ እስር ቤት እስረኞች ያምልጡ አያምልጡ ዘ-ሐበሻ እያጣራች ትገኛለች:: ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም በ እስረኞች ላይ ከባድ ጉዳት ስለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም:: ሆኖም ግን እሳቱ እየተዛመተ ባለበት ወቅት እንኳ እስረኞቹ እሳት እንዳያጠቃቸው ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር ከበላይ ት ዕዛዝ ካልመጣ በስተቀር የአካባቢው ፖሊሶች ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ይነገራል::

********************************************************************************

በአደባባይ ተሰቅሎ ዓመታት ያስቆጠረው የመለስ ዜናዊ ፎቶን የያዘው ትልቅ ፖስተር በዶዶላ ተቃጠለ

http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/02/Meles-zenawi.jpghttp://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/02/Oromo-1.jpg

(ዘ-ሐበሻ) ጃንዋሪ 3 ቀን 2016 ዓ.ም በሰላሌ በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስም የተመሰየመው ፓርክ ሰላሌ ውስጥ በሰልፈኞች ተቃጥሎ ወድሞ ነበር:: ዛሬ ደግሞ ከዶዶላ የመጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ከሞቱ ጊዜ ጀምሮ በከተማዋ ተሰቅሎ የነበረውና የሚያወርደው ጠፍቶ የነበረው ትልቅ ፖስተር በከተማዋ ተቃውሞ በተደረገበት ወቅት ሰልፈኞቹ ፖስተሩን አውርደው በ እሳት አንድደውታል::

የአቶ መለስ ፎቶ ተሰቅሎበት የነበረው ቢልቦርድ ላይም የኦነግ ባንዲራን ሰልፈኞቹ ሰቅለውት ነበር::

ፎቶው ሲቃጠል የተነሳውን ፎቶ ይመልከቱ::

 

Received on Fri Feb 19 2016 - 15:08:54 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved