Ethsat.com: በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ የወጣው ገንዘብ ለትምህርት ከተመደበው ገንዘብ በብዙ እጅ በለጠ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Fri, 11 Sep 2015 00:05:11 +0200

September 10, 2015

ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ የተለያዩ አገራት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2012 ለትምህርት የመደቡትን በጀትና ወደ ውጭ አገራት በህገወጥ መንገድ የወጣውን ገንዘብ በማነጻጸር ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው ፣ በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የወጣው ገንዘብ፣ ለትምህርት ከወጣው ገንዘብ በ245 በመቶ ይልቃል።
ድርጅቱ ቀድም ሲል ባወጣው ሪፖርት ከ2008 እስከ 2012 ባሉት አራት አመታት ውስጥ 3 ቢሊዮን 500 ሚሊዮን ዶላር በህገወጥ መንገድ ወጥቷል። ይህም አገሪቱ ከውጭ ካገኘቸው ገቢ ጋር ሲነጻጸር በ1 ሺ 355 በመቶ ይልቃል።
ግዙፍ የሆነ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ከአገሪቱ መውጣቱ ጥራት ያለው ትምህርት እንዳይሰጥ እንቅፋት መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።
የግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ፕሬዚዳንት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወደ ውጭ በህገወጥ መንገድ የሚወጣውን ገንዘብ ለመቆጣጠር እየወሰደ ያለውን እርምጃ አድንው፣ እርምጃው በመላው አለም በሚገኙ ህጻናት ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ለመቀነስ ይረዳል። ቶጎ፣ ላይቤሪያ፣ ዛምቢያ፣ ቫኑአቱ፣ ቻድ፣ ጉያና፣ ሳሞአ፣ ኒካራጉዋ፣ ፓራጉዋይ፣ አርሜኒያ፣ ማላዊ ከፍተኛ ገንዘብ ወደ ውጭ በህገወጥ መንገድ ከሚወጡባቸው አገራት ተርታ በመሪነት ተጠቅሰዋል።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የከበሩ ማእድናት ሽያጭ ለብዙ ነጋዴዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች የሃብት ምንጭ ሆኗል።

Received on Thu Sep 10 2015 - 18:05:12 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved