Facebook.com: ክፋት በዛ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Tue, 17 Nov 2015 20:27:02 +0100

=====

‪#‎ክፉ_ቀን‬ ‪#‎መንግስት‬ ‪#‎ክፉ_ጋዜጠኖች‬

Watch on the two Videos on the famine in Ethiopia below- 1. The real one and 2. The TPLF propaganda to beautify and hide the famine in Ethiopia.

1. http://www.bbc.com/news/world-africa-34783604

2. http://ethsat.com/video/2015/11/16/esat-daily-news-amsterdam-november-16-2015-ethiopia/

ክፉ ቀን ብዙ ክፉ ምግባሮች ይዞ ይመጣል።

በቀይሽብር ወቅ በመቐለ ከተማ ያጋጠመ እንድ የክፉ ምግባር ምሳሌ ነበር።

ዘስላሰ የተባለ ወጣት በፀረ ደርግነት ተጠርጥሮ የቀይ ሽብር ሰለባ በመሆን በባዛር እየተባለ የሚታወቀውና ኣሁን በስሙ ዘላሰ የተሰየመው የኣፄ ዮውሃንስ ቤተ መንግስት ፊትለፊት የሚገኝ ኣደባባይ ይረሸናል።

ወላጅ እናቱ በደርግ ወታደሮች ተገድደው እልልል እያሉ፣ እያጨበጨቡ ደስታቸው እንዲገልፁ ተደርገዋል።

ያ ቀይ ሽብር ክፉ ቀን የወለደው ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ኣልፈዋል።
ኣሁንም ይሄ ጥቁር ታሪክ ዳግማይ ትንሳኤውን ኣግኝተዋል።

የጥቁር ታራክ ባለቤት የሆነቹ የሰሜን ወሎ ዞን፣ ቆቦ ወረዳ 027 ቀበሌ ኑዋሪ እናት ወይዘሮ ብርቱኳን ዓሊ ነች።

የ5 ዓመት ልጇ በረሃብ ኣጥታ እያነባች ለቢቢሲ የሰጠችው ቃለ ምልልስ ለኢህኣዴግ መንግስት ኣስቆጥቶ ልክ እንደ የዘስላሰ እናት ኣስገድደው እንድታስተባብል ኣድርጓታል።

የኣማራ ክልል ጋዜጠኞች ልክ እንደ የደርግ ወታደሮች ሁሉ ወይዘሮ ብርቱኳን የልጇ ሞት ሃዘን እንዳትችል እያዋከቡና እያስፈራሩ እንድታስተባብል ኣስገደዷት ።

ይባስ ብሎ የኤመሪካ ድምፅ VOA ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩም የወንጀሉ ኣካል መሆኑ እጅግ ያሳዝናል።

ግርማይ ገብሩ የህወሓት መንግስት ሴራ እያወቀው ልጇ በድንገተኛ ሞት እንዳጣች፣ በሬ፣ ላም፣ እህል ወዘተ እንዳገኘባት መዘገቡ ያስገምተዋል። እዚ ላይ የኣማራ ክልል ጋዜጠኞች ያስተላለፉት በቀጣይ ልጆችዋ በረሃብ እንዳታጣ መስጋትዋ ገልፃለች። ግርማይ ግን ከነሱ ብሶ መዘገቡ ያሳዝናል።

የትግራይ ገበሬ 100% ሞዴል፣ የኣንድ ዓመት ምርት 113 ሚልዮን ኩንታል ኣመረተ ብሎ የሚዋሽ ድርጅ መሆኑ እያወቀና ጋዜጠኞች እንደሚሄዱ ኣውቀው የጠቀሳቸው ከብቶችና እህል ኣስቀድመው በቤትዋ ማስቀመጥ እንዴት ያቅታቸዋል ብሎ ያስባል?

ቅለል ያለው ………ሆነ እንጂ የቢቢሲ መግለጫዋ ያስኮነነ መንግስ UN በየቀኑ ሁለት ሰዎች ድርቅ ባስከተለው ረሃብ እየሞቱ እንዳሉ ገልፀዋል።

የቀይ ሽብር ተግባር በድርቅ ሲደገም እጅጉን ያማል።

 

Received on Tue Nov 17 2015 - 14:27:04 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved