Ecadforum.com: የጄት ድብደባ ወይንስ የአውሮፕላን መከስከስ?

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Tue, 24 Mar 2015 23:21:21 +0100

የጄት ድብደባ ወይንስ የአውሮፕላን መከስከስ?

March 24, 2015

አበበ ገላው (ከፌስቡክ የተወሰደ)

ወያኔ ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ አንድ የካናዳ የወርቅ ማእድን በአውሮፕላን መደብደቡን አፍቃሪ ወያኔ የሆኑ ድረ ገጾች “ወታደራዊ ምንጮችን” በመጥቀስ ዘግበዋል።

ይሁንና እንኳን ድብደባው የጥቃቱን ውጤት ያሳያል ተብሎ የተለቀቀውም ፎቶ የውሸት መሆኑ ተረጋግጧል። አውራንባ ታይምስ አስተማማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ድብደባውን ማረጋገጡን የዘገበ ሲሆን ዘገባውም በፎቶ ማስረጃ የታጀበ ነው። ይሁንና ፎቶው የሚያሳው ኤርትራ ውስጥ የተኪያሄደውን የአየር ጥቃት ውጤት ሳይሆን ቢቢሲ በኦገስት 9 2013 አንድ የወያኔ አየር ሃይል የእቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን ሞቃዲሹ ውስጥ ተከስክሶ ሲጋይ የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃን ነው። ይህም ፎቶ የተነሳው በሮይተርስ ሲሆን በቢቢሲ ድረ ገጽ ላይ ከዜናው ጋር በክብር ታትሞ ይገኛል።

Ethiopian Air Force Jets Attack

አውራምባ ታይምስ ግን ዜናውን እውነት ለማስመሰል ከርክሞ እውነተኛውን ምንጭ ሳይጠቅስ ለታዳሚዎቹ አቅርቧል። በዚህም ጥፋት የሚያሳይ ፎቶ የተደነቁ በርካታ ወያኔዎች “አየር ሃይሉን” በማወደስ አስተያየት ሰንዝረዋል። የካናዳው የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ካምፓኒ ግን አንዳንድ ሰራተኞቹ የተወሰኑ ማሽኖች ሆን ብለው ማበላሸታቸውን እና ጥገና አድርጎ ስራ መቀጠሉን በይፋ ገልጿል።

መቼም አንድ ጋዜጠኛ በጄት ድብደባና በአውሮፕላን ወድቆ መከስከስ መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ ይገነዘባል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። አውራምባ ታይምስ ላይ በጭስ ተሸፍኖ የሚታየው ከተማ ሞቃዲሹ እንጂ አስመራ አለመሆኑን ከቢቢሲ ዘገባ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ነው ወይንስ ሶማሊያና ኤርትራ ሳንሰማ “ያለምንም ቅደመ ሁኔታ” ተዋሃዱ?

ለማንኛውም ቢቢሲ የአውሮፕላን መከስከስን አስመልክቶ ያቀረበው ዘገባ እስከ ፎቶው እዚህ ገጽ ላይ ይገኛል።
http://www.bbc.com/news/world-africa-23628549

(ይህንን ጥቆማ ያቀረበውን አንድ ወዳጃችንን ሳላመሰግን አላልፍም)

Received on Tue Mar 24 2015 - 18:21:21 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved