Goolgule.com: የጦፈ ሙስና ከመንገድ ሥራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከቤቶች ልማት

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Wed, 25 Feb 2015 21:04:43 +0100

የጦፈ ሙስና ከመንገድ ሥራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከቤቶች ልማት

በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ ነው - ሚኒስትሩ
lightrail road

* ከ30 እስከ 40% የግንባታ ወጭ ይዘረፋል!!

የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል።

የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሷል። የአደጋ መከላከያ ብረቶች የተሰሩት ከወጣላቸው የጥራት ደረጃ በሶስት እጅ ያነሱ ሆነው በመገኘታቸው ጉዳዩ ለቦርድ ሰብሳቢው አርከበ እቁባይ ቢቀርብም ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገባ ማወቅ አለመቻሉን ገልጿል።

የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን ያቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትር መኩሪያ ሃይሌ፣ ችግሩ የተፈጠረው ለምርጫው ሲባል የባቡሩ ግንባታ እንደ ትልቅ የምርጫ ማሳመኛ በመያዙ ነው ።

የግንባታ ኢንዱስትሪው ከሚያወጣው ወጪ ከ30 እስከ 60 በመቶ የሚሆነው በሙስና ይባክናል ሲሉም ሚኒስትሩ አክለዋል።

እንደዚያም ሆኖ በቅርቡ የተመረቀ የአዲስ አበባ መለስተኛ የባቡር ግንባታ፣ አገልግሎት ከመጀመሩ ከወዲሁ በርካታ የመፈራረስ ችግሮች እያጋጠሙት ነው። ለፖለቲካ ፍጆታና ለፕሮፓጋንዳ ሲባል ቶሎ ቶሎ እንዲሰራ ከማድረግ ዉጭ እነ አቶ አርከበ እቁባይ የሕዝቡን ፍላጎት ከግምት ያላስገቡ ሲሆን፣ አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች አልተወሰዱም። በዋናነት የባቡ ሃዲዱ ከተማዋን ለሁለት የከፈለ ሲሆን ከሃዲዱ በስተቀኝ እና በስተግራ ያሉ ነዋሪዎች ለመገናኘት እጅግ በጣም ብዙ ርቀት ለመጓዝ ተገደዋል።

Received on Wed Feb 25 2015 - 15:04:47 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved