Ethsat.com: ሄሊኮፕተር ጠልፈው የተሰወሩት በመልካም ሁኔታ ላይ ናቸው ተባለ

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sat, 27 Dec 2014 16:29:54 +0100

ሄሊኮፕተር ጠልፈው የተሰወሩት በመልካም ሁኔታ ላይ ናቸው ተባለ

December 27, 2014

 

ታኀሳስ ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአየር ሃይል ባልደረባ የሆኑት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ ከበረራ ቴክኒሻኑ ጸጋ ብርሃን ግደይ ጋር በጋራ በመሆን የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ከጠፉ በሁዋላ በአሁኑ ጊዜ በምልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የኢሳት ምንጮች ግልጸዋል።

 

ምንጮቹ አብራሪዎቹ ያሉበትን ቦታ ለመግለጽ ፈቃደኛ ባይሆኑም፣ በአሁኑ ጊዜ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

 

ኢሳት አብራሪዎቹን ለማነጋገር ጥረቱን አሁንም በመቀጠል ላይ ነው።

 

በአየር ሃይል ውስጥ የሚካሄደው ግምገማ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን፣ በድሬዳዋ የአየር ላይ በረራ ልምምድ እንዲቋረጥ ከተደረገ በሁዋላ እስካሁን ልምምድ አልተጀመረም። በደብረዘይት አየር ሃይል ግቢ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት እንዳለም የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

 

መንግስት አብራሪዎቹ ኤርትራ ገብተዋል ቢልም፣ በኤርትራ በኩል እስካሁን የተሰጠ መልስ የለም። አብራሪዎቹ ይዘውት የጠፉት ተዋጊ ሄሊኮፕተር ዘመናዊና እጅግ ውድ መሆኑን መረጃዎች የመለክታሉ።

 

የኢህአዴግ መንግስት የጠፉትን አብራሪዎችና ሄሊኮፕተሩን በተመለከተ ተከታታይ መግለጫዎችን ከመስጠት ተቆጥቧል።

Received on Sat Dec 27 2014 - 10:29:56 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved