Goolgule.com: ኢህአዴግ በባህር ዳር ግድያ ፈጸመ! በባህርዳር ዋይታ ሆነ!

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Wed, 24 Dec 2014 16:35:04 +0100

ኢህአዴግ በባህር ዳር ግድያ ፈጸመ!

በባህርዳር ዋይታ ሆነ!

 

December 21, 2014 03:32 am

በእምነት ቦታ ይገባኛል ነዋሪዎች ባሰሙት ጥያቄ ኢህአዴግ የጥይት መልስ ሰጠ፡፡ ድርጊቱን በምስል በማያያዝ በተለያዩ ማኅበራዊ ገጾች ያሰራጩት ክፍሎች አዛውንትና መነኮሳት ሳይቀሩ መደብደባቸውንና መቁሰላቸውን በምስል አስደግፈው አመልክተዋል፡፡

አኻዙ በትክክለኛው ባይታወቅም አምስት የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ በማኅበራዊ ገጾች የተበተኑት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንዳንድ የድረገጽ ዜናዎችም በአኻዝ ከመለያየት በስተቀር የግድያውንና የድብደባውን መጠን በመግለጽ ዜናቸውን አስፍረዋል፡፡

ድርጊቱን የፈጸመው ኢህአዴግ ስለሞቱትና ስለተደበደቡት መነኮሳትና አዛውንት እንዲሁም ሌሎች ወገኖች ይህንን መረጃ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ይፋዊ ማስተባበያ አልሰጠም፡፡ ይልቁንም ከሁለት ሳምንት በፊት ኢህአዴግ የፌዴራል ምክት ሚ/ሩን በፖሊስ ፕሮግራም በማቅረብ የፌስቡክ ዜናዎችን አትመኑ በማለት ማሳሰቢያ ሲሰጥ ነበር፡፡

“ <https://www.facebook.com/negere.ethiopia> ነገረ ኢትዮጵያ” የተሰኘው የፌስቡክ ገጽ ቀበሌ፣ ወሰንና የምክርቤት ስም ጠቅሶ የተፈጠረውን ሁኔታ ከዚህ እንደሚከተለው አስፍሮታል፡፡...............................

ኣብ‘ዚ ታሕቲ ዘሎ ስቱር ሕጥበ-ጽሑፍ (PDF) ጠዊቕኩም ዝርዝራቱ ኣንብቡ፣

ብርሃነ ሃብተማርያም

 

 




Received on Wed Dec 24 2014 - 10:36:14 EST

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved