[Dehai-WN] Zehabesha.com: ግልጽ መልእክት ለአገራችን የታሪክ ፀሃፊዎችና ፖለቲከኞች ! ክፍል 1-2 [ንክልቲኡ ክፋላት ብምሉኡ ብኽብረትኩም አብ "ፒዲፍ" አንብብዎ ኢኹም]

From: Berhane Habtemariam <Berhane.Habtemariam_at_gmx.de_at_dehai.org>
Date: Sat, 8 Jun 2013 23:32:24 +0200


ግልጽ መልእክት ለአገራችን የታሪክ ፀሃፊዎችና ፖለቲከኞች !


የታሪክ ተወቃሽነቱን ከራሳችን እንጀምር !

በመንገሻ ሊበን []

08.06.2013

እኛ ኢትዮጵያዊያን የአኩሪ ታሪክ ባለቤቶች እንደሆን ከልጅነት እድሜያችን ጀምሮ እየተነገረን ያደግን ህዝቦች ነን ። የሰው ልጅ መገኛ ፤የቅዱሳን አገር ፤የጀግኖች መፍለቂያ ምድር ፤ መቅደላ ፤አድዋ፤ ማይጨው ወ.ዘ.ተ የሚሉት ቃላት በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አእምሮ ውስጥ የሚያቃጭሉ የታሪክ ፀፊዎቻችን የብእር ትሩፋቶች ናቸው ። እጅግ የሚገርመው ግን ፣ የአፄ ቴድሮስ እጅና እግር ቆራጭነት ፤ የአፄ ዮሃንስ አንገት ቀንጣሽነት የአፄ ምኒልክ ጡት ዘልዛይነት እንደዚሁም የአፄ ኃይለስላሴ ፤ የኮሎኔል መንግስቱና የአቶ መለስ ዜናዊ አሰቃቂ ወንጀሎች የታሪካችን አንድ አካል መሆናቸው እየታወቀ በታሪክ ፀሃፊዎቻችን ዘንድ ግን ብዙም የሚዳሰሱ ነገሮች አለመሆናቸው ነው ።

እንደዚህ ፅሁፍ አቅራቢ እምነት ፣ መልካሙን ታሪካችን እንዴት አቅበን መጓዝ እንዳለብንና ከመጥፎ ታሪካችንም ምን ዓይነት ልምድ መቅሰም እንደሚገባን መማር የምንችለው ታሪክ ፀሃፊዎቻችን ትክክለኛውን ታሪካችንን ያለምንም መዛነፍና ወገንተኝነት በሃቀኛ ብእራቸው ሲከትቡልን ብቻ ነው ።መረረም ጣፈጠም የኛ ታሪክ የኛ የራሳችን ነውና ።

ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩ በቀጣይነት ላነሳው ወደፈለኩት ርዕሰ ጉዳይ ላምራ።

አውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች እንደ ቅርጫ በተከፋፈሏት የጥቁሮች ምድር፣ በጀግኖች አባቶቻቸን ከፍተኛ መስዋእትነት ብቸኛዋ የነፃነት ቀንዴል የሆነችው እናት አገራችን ኢትዮጵያ፣ ካለፉት 50 እና 60 ዓመታት በተለይም ደግሞ ካለፉት 22 ዓመታት ወዲህ እያጋጠማት ያለው ህልውናዋን የሚፈታተን ኩነት የቱን ያህል ከባድና አሳሳቢ እንደሆነ ብዙዎቻችን የምንገነዘበው ነገር ይመስለኛል።

እንደ እኔ እምነት ለዚህ የአገርን ህልውና በቀጣይነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየጣለ ለሚገኘው የተወሳሰበ ችግር ተጠያቂዎቹ፣ ከ1983 በኋላ መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠረው የወያኔ ስርዓትና ከእርሱ በፊት የነበሩት ሁለት መንግስታት ብቻ ሳይሆኑ፣ የሃገራችን ታሪክ ፀሃፊዎች፤ ሙሉ እድሜያቸውን በተቃዋሚነት ጎራ ተሰልፈናል የሚሉ ሃይሎችና የኢትዮጵያን ችግር እንደ እጃችን መዳፍ ጠንቅቀን እናውቀዋልን እያሉ በየአደባባዩ የሚመፃደቁት ፖለቲከኞቻችን ጭምር ናቸው።

በእርግጥም እነዚሁ ሃይሎችና ተመፃዳቂ ግለሰቦች ፣ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፣ ያልነበረን ታሪክ የነበረ አስመስሎ በማቅረብና ፣ “ታሪክ እንደፀሃፊው ነው” እንዲሉ ፣ ከሞላ ጎደል ሁሉንም ታሪካችንን

(መጥፎም ይሁን ጥሩ ታሪክ )

ለፀሃፊው ወይም ለገዥው አካል በሚመች መንገድ በማቅረብ ፣ አንዳንዴም ኢምንቱን ፍፃሜ እጅግ በተጋነኑ የማንህሎኝነት ቃላት በመጀቦን ወይም ደግሞ ትውልድ ሊማርበት የሚገባውን አንኳር ፍፃሜ ምንም እንዳልተፈፀመ በማስመሰል፣ አላስፈላጊ የህይወትና የጊዜ መስዋእትነት እንድንከፍል ከማድረጋቸውም በላይ … በአገራችን ኢትዮጵያ ላይም አሳፋሪ ውድቅት እንዲከተልና ትውልድም ያለፈ ታሪኩን በሚገባ እንዳይገነዘብ የየራሳቸውን ድርሻ አበርክተዋል ብቻ ሳይሆን እስከ ዛሬም እያበረከቱ ይገኛሉ ።

ስለሆነም ታሪክን በማፋለስ ረገድ ፣ የታሪክ ተወቃሽነቱ መጀምር ያለበት፣ ይህንን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተፈጸመ በደል ይፋ አውጥቶ በግልፅ በመወያየትና በመመካከር እንጅ፣ በተፋለሰ ታሪክ ላይ ተንተርሶ በጥፋት ላይ ጥፋት በመስራት አልያም ደግሞ የራስን ሌባ ጣት ወደ ሌላ በመቀሰርና ተጠያቂነቱን በሌሎች ላይ በመለደፍ መሆን የለበትም።

እንደሁሉም የአለም አገራት ፣ አገራችን ኢትዮጵያም በተለያዩ ፍፃሜዎች መጥፎና ደግ ኩነቶችን ያስተናገደች ምድር ናት ። ይህ ሁለት ተፃራሪ ኩነት በታሪክ መዝገብ ላይ በሚገባ ሊሰፍርና ትውልድም በጥልቀት ሊማርበት የሚገባው ነገር ይመስለኛል ። አስቀድሜ በፅሁፌ መግቢያ ላይ እንደጠቀስኩት ከመጥፎ ታሪካችን ምን ዓይነት ልምድ መቅሰም እንደሚገባንና መልካሙን ታሪካችን ደግሞ እንዴት አቅበን መጓዝ እንዳለብን መማር የምንችለው ታሪካችን ያለምንም መዛነፍና ወገንተኝነት በሃቀኛ ፀሃፊዎች ተከውኖ ሲቀርብልን ብቻ ነው። ከዚያ ውጭ ግን መነገር ያለበት ሃቀኛው ታሪካችን በግለሰቦችና የፖለቲካ ሃይሎች አስተሳሰብ ፤ ስሜትና ፍላጎት ላይ ብቻ ተመርኩዞ መፃፉን ከቀጠለ ፣ የታሪክ መፋለስ እንዳያስከትል በእጅጉ ሊያሰጋን የሚገባ ነገር ነው ።

ለመንደርደርያ ያህል አንድ አንኳር ነጥብ ላንሳ ። ይህ አንኳር ነጥብ ፣ ላለፉት 50 እና 60 ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ዓመታት ፣ የህዝባችንና የፖለቲካ ሃይሎቻችንን ቀልብ በከፍተኛ ደረጃ ከሳቡት የአገራችን የፖለቲካ አጀንዳዎች መካከል አንዱ ነው። ይህ አንኳር ጉዳይ በአገራችን የታሪክ መዝገብ ላይ ያለምንም መዛነፍና ወገንተኝነት በሚገባ ሰፍሯልን…?

ወይም ደግሞ ከእስካሁኑ ፍፃሜ በኋላስ ትውልድ ሊማርበት የሚገባው ሃቀኛ ታሪክ ያለወገንተኝነት እየተፃፈ ነውን…..? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይሰጥበት ዘንድ አንባቢን በአክብሮት እጋብዛለሁ ።

ሁሉም እንደሚያውቀው በአገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻን ከሚይዙት አንኳር ጉዳዮች መካከል አንዱ የኤርትራ ጉዳይ ነው።...........................................................

ሓበሬታ: ንክልቲኡ ክፋላት ብምሉኡ ብኽብረትኩም አብ „ፒዲፍ“ አንብብዎ ኢኹም::

 





      ------------[ Sent via the dehai-wn mailing list by dehai.org]--------------

Received on Sun Jun 09 2013 - 20:48:00 EDT

Dehai Admin
© Copyright DEHAI-Eritrea OnLine, 1993-2013
All rights reserved